የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:7-18

1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:7-18 መቅካእኤ

ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚያፈቅር ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፥ እግዚአብሔርንም ያውቃል። የማያፈቅር እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። በዚህም የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል እንድንኖር እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና። ፍቅር በዚህ ነው፥ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን ነገር ግን እርሱ እንደ ወደደን እና ለኃጢአታችንም ማስተስሪያ እንዲሆን ልጁን ስለላከልን ነው። ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፥ እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል። እግዚአብሔርን ያየው ማንም የለም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፥ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል። በእርሱ እንደምንኖር እሱም በእኛ እንደሚኖር በዚህ እናውቃለን፥ ምክንያቱም ከመንፈሱ ስለ ሰጠን ነው። አብ ወልድን የዓለም አዳኝ እንዲሆን እንደ ላከው አይተናል፥ እንመሰክራለንም። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚመሰክር ሁሉ፥ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል። ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነናልም። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፥ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል። በፍርድ ቀን ድፍረት እንዲኖረን ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ ምክንያቱም እርሱ እንደሆነ እኛ ደግሞ በዚህ ዓለም እንዲሁ ነን። በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ነገር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፤ ፍርሃት ቅጣት አለው፥ የሚፈራ ሰው በፍቅር ፍጹም አልሆነም።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}