እነርሱም እንደገና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ በዚህ ጊዜ ዖርፋ ዐማትዋን ስማ ተሰናበተች፤ ሩት ግን ከዐማትዋ ላለመለየት ወሰነች። ስለዚህ ናዖሚ “ሩት ሆይ! የባልሽ ወንድም ሚስት ወደ ወገኖችዋና ወደ አማልክትዋ ተመልሳለች፤ አንቺም ከእርስዋ ጋር ተመለሺ” አለቻት። ሩት ግን እንዲህ አለቻት፦ “ተለይቼሽ እንድመለስ አታስገድጅኝ! አንቺ ወደምትሄጂበት ሁሉ እሄዳለሁ፤ አንቺ በምትኖሪበት እኖራለሁ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤ በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ በምትቀበሪበትም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር ከአንቺ የሚለየኝ ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ይፍረድብኝ!” ሩት ከእርስዋ ጋር ለመሄድ ቊርጥ ሐሳብ ማድረጓን በተረዳች ጊዜ፥ ናዖሚ ሌላ ነገር አልተናገረችም።
መጽሐፈ ሩት 1 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ሩት 1:14-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
YouVersion የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን ይጠቀማል። የእኛን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በግለሰብነት መመሪያችን ላይ እንደተገለጸው የእኛን የኩኪዎች አጠቃቀም ተቀብለዋል
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች