ወደ ሮም ሰዎች 9:10-15

ወደ ሮም ሰዎች 9:10-15 አማ05

ይህም ብቻ ሳይሆን ርብቃ የነገድ አባታችን ከሆነው ከይስሐቅ መንታ ልጆችን በፀነሰች ጊዜ፥ የእግዚአብሔር ምርጫ በሥራ ሳይሆን በጥሪ መሆኑን ለመግለጥ ሁለቱ ልጆች ከመወለዳቸውና ክፉም ሆነ ደግ ከማድረጋቸው በፊት እግዚአብሔር ርብቃን “ታላቁ ለታናሹ ተገዢ ይሆናል” አላት። ይህም “ያዕቆብን ወደድኩ ዔሳውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ያዳላል ማለት እንችላለን? እግዚአብሔር ያዳላል ማለትስ ከቶ አንችልም! እግዚአብሔር ሙሴን “ልምረው የምፈልገውን እምረዋለሁ፥ ልራራለት የምፈልገውንም እራራለታለሁ” ብሎታል።