ሕግ መንፈሳዊ መሆኑን እናውቃለን። እኔ ግን የኃጢአት ባሪያ ለመሆን የተሸጥሁ ሥጋዊ ነኝ። እኔ የማደርገውን አላውቅም፤ የምወደውን ነገር ማድረግ ትቼ የምጠላውን ነገር አደርጋለሁ። እንግዲህ እኔ የማደርገው የማልፈልገውን ነገር ከሆነ ሕግ መልካም እንደ ሆነ እመሰክራለሁ። ማድረግ የማልፈልገውን ነገር የሚያደርገው በእኔ ውስጥ ያለው ኃጢአት ነው እንጂ እኔ አይደለሁም። በእኔ ወይም በእኔ ሥጋዊ ባሕርይ ምንም መልካም ነገር እንደሌለ ዐውቃለሁ፤ መልካም ነገርን የማድረግ ፍላጎት ቢኖረኝም እንኳ ያን መልካም ነገር ለማድረግ ችሎታ የለኝም። ማድረግ የምፈልገውን መልካም ነገርን አላደርግም፤ ዳሩ ግን የማልፈልገውን ክፉ ነገር አደርጋለሁ። ማድረግ የማልፈልገውን ክፉ ነገር የማደርግ ከሆንኩ ይህን የሚያደርገው በእኔ ውስጥ ያለው ኃጢአት ነው እንጂ እኔ አይደለሁም ማለት ነው።
ወደ ሮም ሰዎች 7 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ሮም ሰዎች 7:14-20
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos