ፌቤ በክንክሪያ ከተማ ቤተ ክርስቲያንን የምታገለግል ታማኝ እኅታችን መሆንዋን እንድታውቁ እወዳለሁ። እርስዋ እኔንና ሌሎችንም ብዙ ሰዎች የረዳች ስለ ሆነች ምእመናን እንግዶችን መቀበል እንደሚገባቸው ዐይነት በጌታ ስም ተቀብላችሁ በሚያስፈልጋት ነገር ሁሉ እንድትረዱአት ዐደራ እላችኋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ተባባሪዎቼ ለሆኑት ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱ በእኔ ምትክ ለመሞት እንኳ የተዘጋጁ ነበሩ፤ በዚህም ዘወትር አመሰግናቸዋለሁ፤ እኔም ብቻ ሳልሆን ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና የተመለሱ ምእመናን አብያተ ክርስቲያን ጭምር ያመሰግኑአቸዋል። በእነርሱ ቤት ለጸሎት ለሚሰበሰቡት ምእመናንም ሰላምታ አቅርቡልኝ። በእስያ ክፍለ ሀገር በመጀመሪያ በክርስቶስ ላመነውና ለምወደው ለኤጴኔጦስ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ለእናንተ ብዙ ለደከመችው ለማርያም ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእኔ ጋር ታስረው ለነበሩና በሐዋርያትም መካከል ታዋቂዎች ለነበሩት አይሁድ ዘመዶቼ፥ ለአንድሮኒቆስና ለዩኒያስ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱ በክርስቶስ በማመን እኔን ይቀድሙኛል። በጌታ ለምወደው ለአምጵልያቶስ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ በክርስቶስ ሥራ ተባባሪያችን ለሆነው ለዑርባኖስና ለምወደውም ለእስጣኩስ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በክርስቶስ መሆኑ ተፈትኖ ለተመሰከረለት ለአጴሊስ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ ከአርስጦቡሎስ ቤተሰብ ለሆኑትም ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ ለአይሁዳዊው ዘመዴ ለሄሮድዮን ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ ከናርሲሰስ ቤተ ሰዎች በጌታ ላመኑት ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ አገልግሎት ለሚደክሙት ለትሩፋይናና ለትሩፎሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ አገልግሎት እጅግ ለደከመችውና በክርስቶስ ለምወዳት ለፔርሲስ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ጌታን በማገልገል በጣም ለታወቀው ለሩፎስ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እኔን እንደ ልጅዋ ትወደኝ ለነበረችው ለእናቱም ሰላምታ አቅርቡልኝ። ለአስንክሪቶስና ለፍሌጎን፥ ለሄርሜስም፥ ለፓትሮባስም፥ ለሄርማስም፥ ከእነርሱም ጋር ላሉ ወንድሞች ሰላምታ አቅርቡልኝ። ለፊሎሎጎስ፥ ለዩልያ፥ ለኔርያና ለእኅቱም ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እንዲሁም ለኦሉምፓስና ከእነርሱም ጋር ላሉ ምእመናን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በተቀደሰ መሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ። የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
ወደ ሮም ሰዎች 16 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ሮም ሰዎች 16:1-16
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች