የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮሐንስ ራእይ 5

5
መጽሐፉና በጉ
1በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ቀኝ እጅ፥ በውስጥና በውጪ የተጻፈበት በሰባት ማኅተም የታሸገ የብራና ጥቅል መጽሐፍ አየሁ፤ #ሕዝ. 2፥9-10፤ ኢሳ. 29፥11። 2አንድ ብርቱ መልአክ በታላቅ ድምፅ “ማኅተሞቹን መፍታትና የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ መክፈት የሚገባው ማን ነው?” ብሎ ሲናገር አየሁ። 3ነገር ግን በሰማይም ሆነ በምድር ወይም ከምድር በታች የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ መክፈትና ውስጡን መመልከት የተቻለው ማንም አልነበረም። 4የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ መክፈትና ውስጡን መመልከት የሚገባው ስላልተገኘ በጣም አለቀስኩ፤ 5በዚያን ጊዜ ከሽማግሌዎቹ አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው ከዳዊት የትውልድ ሐረግ የተነሣ አንበሳ ድል ነሥቶአል፤ እርሱ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍና ሰባቱን ማኅተሞች መክፈት ይችላል” አለኝ። #ዘፍ. 49፥9፤ ኢሳ. 11፥1፤10።
6ከዚህ በኋላ በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከል፥ በሽማግሌዎችም መካከል የታረደ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ፤ ይህ በግ ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤ እነርሱ ወደ ዓለም ሁሉ የተላኩ ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው። #ኢሳ. 53፥7፤ ዘካ. 4፥10። 7በጉ መጣና በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ወሰደ፤ 8የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ኻያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት በግንባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸው በገና ይዘው ነበር፤ እንዲሁም የቅዱሳን ጸሎት የሆነው ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሙዳይ ይዘው ነበር። #መዝ. 141፥2። 9አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦
“በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥
ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ
ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥
አንተ ስለ ታረድህ
የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና
ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤ #መዝ. 33፥3፤ 98፥1፤ ኢሳ. 42፥10።
10ለአምላካችንም የካህናት መንግሥት
እንዲሆኑ አድርገሃቸዋል፤
በምድርም ላይ ይነግሣሉ።” #ዘፀ. 19፥6፤ ራዕ. 1፥6።
11ወደዚያም ስመለከት በዙፋኑና በእንስሶቹ በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ብዛታቸውም በብዙ ሺህና በብዙ ሚሊዮን የሚቈጠር ነበር፤ #ዳን. 7፥10። 12በታላቅ ድምፅም፥
“የታረደው በግ ኀይልን፥ ሀብትን፥
ጥበብን፥ ብርታትን፥ ገናናነትን፥ ክብርንና
ምስጋናን ለመቀበል የሚገባው ነው” አሉ።
13በሰማይና በምድር፥ ከምድር በታችና በባሕር፥ በውስጣቸውም ፍጥረቶች ሁሉ
“በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለበጉም
ምስጋና፥ ገናናነት፥ ክብርና ኀይል
ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን!” ሲሉ ሰማሁ።
14አራቱ እንስሶችም “አሜን!” አሉ፤ ኻ አራቱ ሽማግሌዎችም በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ