የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮሐንስ ራእይ 19:6-9

የዮሐንስ ራእይ 19:6-9 አማ05

የብዙ ሰዎችን ድምፅ የወራጅ ውሃን ድምፅ፥ የብርቱ ነጐድጓድንም ድምፅ፥ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚችል ጌታ አምላካችን ይነግሣል! የበጉ ሠርግ ስለ ደረሰና የእርሱም ሙሽራ ስለ ተዘጋጀች ኑ ደስ ይበለን! ደስታም እናድርግ! እናክብረውም! የሚያንጸባርቅና ንጹሕ የሆነ ውብ ልብስ እንድትለብስ ተሰጣት፤ ቀጭኑ ልብስ የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነው።” ከዚህ በኋላ መልአኩ “ወደ በጉ ሠርግ ግብዣ የተጠሩ የተባረኩ ናቸው” ብለህ ጻፍ አለኝ፤ ቀጥሎም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው” አለ።