የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮሐንስ ራእይ 15

15
የመጨረሻዎቹን መቅሠፍቶች የያዙ መላእክት
1ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቊጣ የሚፈጸምባቸውን የመጨረሻ የሆኑትን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙትን ሰባት መላእክት አየሁ።
2ከዚህ በኋላ እሳት የተቀላቀለበት የመስተዋት ባሕር የሚመስል ነገር አየሁ፤ እንዲሁም አውሬውንና የአውሬውን ምስል፥ የስሙንም ቊጥር ምልክት ድል የነሡትን አየሁ፤ እግዚአብሔር የሰጣቸውን በገና ይዘው በመስተዋቱ ባሕር አጠገብ ቁመው ነበር። 3የእግዚአብሔርን አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፥
“ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ!
ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው፤
የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ!
መንገድህ ትክክልና እውነት ነው፤ #15፥3 የሕዝቦች ንጉሥ፦ አንዳንድ ቅጂዎች “የዘመናት ንጉሥ” ይላሉ። #ዘፀ. 15፥1።
4ጌታ ሆይ! አንተን የማይፈራና
ስምህንም የማያከብር ማን ነው?
አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ፤
የእውነት ፍርድህ ስለ ተገለጠ፥
ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።” #ኤር. 10፥7፤ መዝ. 86፥9።
5ከዚህም በኋላ ተመለከትኩ፤ እነሆ፥ የምስክር ድንኳን የሆነው ቤተ መቅደስ በሰማይ ተከፈተ፤ #ዘፀ. 38፥21። 6ሰባቱን መቅሠፍቶች የያዙት ሰባቱ መላእክት ከቤተ መቅደሱ ወጡ፤ ንጹሕ የሚያንጸባርቅ ነጭ በፍታ ለብሰው ነበር፤ ደረታቸውንም በወርቅ መታጠቂያ ታጥቀው ነበር። 7ከአራቱ እንስሶች አንዱ ለሰባቱ መላእክት ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የሚኖረው የእግዚአብሔር ቊጣ የመላባቸውን ሰባት የወርቅ ጽዋዎች ሰጣቸው። 8ቤተ መቅደሱም ከእግዚአብሔር ክብርና ኀይል የተነሣ በጢስ ተሞላ፤ ሰባቱ መላእክት የያዙአቸው ሰባት መቅሠፍቶች እስከ ተፈጸሙ ድረስ ማንም ወደ ቤተ መቅደሱ መግባት አልቻለም። #ዘፀ. 40፥34፤ 1ነገ. 8፥10-11፤ 2ዜ.መ. 5፥13-14፤ ኢሳ. 6፥4።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ