ሌላ አውሬ ደግሞ ከምድር ሲወጣ አየሁ፤ እንደ በግ ሁለት ቀንዶች ነበሩት፤ አነጋገሩም እንደ ዘንዶው ነበር፤ የመጀመሪያውን አውሬ ተክቶ በእርሱ ሥልጣን ይሠራ ነበር፤ ምድርና በእርስዋ ላይ የሚኖሩት ሁሉ ለመጀመሪያው አውሬው እንዲሰግዱ አደረገ፤ ይህም አውሬ ያ ለሞት የሚያደርስ ቊስል የዳነለት የመጀመሪያው አውሬ ነው። ይህ ሁለተኛው አውሬ ግን በሰዎች ፊት እሳትን ከሰማይ እስከማውረድ ድረስ ታላላቅ ተአምራትን ያደርግ ነበር። በመጀመሪያው አውሬ ፊት እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተአምራት ምክንያት በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር፤ በሰይፍ ቈስሎ ለዳነው ለአውሬው ክብር ምስል እንዲሠሩም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዛቸዋል። ሁለተኛው አውሬ ለመጀመሪያው አውሬ ምስል የሕይወት እስትንፋስ ለመስጠት ሥልጣን ተሰጠው፤ የሕይወት እስትንፋስ ለመስጠት ሥልጣን የተሰጠውም ምስሉ ለመናገር እንዲችልና ለእርሱ የማይሰግዱት ሁሉ እንዲገደሉ ያደርግ ዘንድ ነው። ሁለተኛው አውሬ ታናናሾችም ሆኑ ታላላቆች፥ ሀብታሞችም ሆኑ ድኾች፥ ጌቶችም ሆኑ አገልጋዮች፥ ሁሉም በቀኝ እጃቸው ወይም በግንባራቸው ላይ ምልክት እንዲያደርጉ አስገደዳቸው። በዚህ ዐይነት የአውሬውን ስም የሚያሳይ ምልክት ወይም የስሙ ቊጥር የሌለው ማንም ሰው መግዛትም ሆነ መሸጥ አይችልም። ጥበብ የሚፈለገው እንግዲህ እዚህ ላይ ነው፤ አእምሮ ያለው የአውሬውን ቊጥር ያስላው፤ ቊጥሩ የሚያመለክተው ሰውን ነው፤ ቊጥሩም ስድስት መቶ ሥልሳ ስድስት ነው።
የዮሐንስ ራእይ 13 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ራእይ 13:11-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos