የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 90:9-13

መጽሐፈ መዝሙር 90:9-13 አማ05

ዘመናችን ሁሉ በቊጣህ ያልፋሉ የዕድሜአችንም ፍጻሜ እንደ እስትንፋስ ነው። ዕድሜአችን ሰባ ዓመት ነው፤ ቢበዛም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ እነዚያም ዘመናት በችግርና በሐዘን የተሞሉ ናቸው፤ ዕድሜአችን በቶሎ ያልቃል፤ እኛም እናልፋለን። አንተን የሚፈሩ ሰዎች ቊጣህን የሚረዱትን ያኽል፥ የአንተን የቊጣ ኀይል የሚያውቅ ማነው? ጥበበኞች ለመሆን እንድንችል ዕድሜአችን ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ አስተምረን። እግዚአብሔር ሆይ! ቊጣህ እስከ መቼ ይቈያል? እባክህ ለአገልጋዮችህ ራራ!