እግዚአብሔር ሆይ! ምሕረትን አድርግልኝ! ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት! ከሞትም አድነኝ። ይህን ብታደርግልኝ፥ በጽዮን አደባባይ፥ ምስጋናህን ሁሉ ለሕዝብ እናገራለሁ፤ ስላዳንከኝም ደስታዬን እገልጣለሁ። አሕዛብ በቈፈሩት ጒድጓድ ወደቁ፤ በደበቁት ወጥመድ ተያዙ። እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ። ክፉዎች ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ። እግዚአብሔርንም ከረሱ ሕዝቦች ጋር ይቀላቀላሉ። ችግረኞች ዘወትር እንደ ተረሱ አይቀሩም፤ የድኾችም ተስፋ ከንቱ ሆኖ ለዘለዓለም አይጠፋም።
መጽሐፈ መዝሙር 9 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 9:13-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች