የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 9:1-6

መጽሐፈ መዝሙር 9:1-6 አማ05

አምላክ ሆይ! በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ያደረግኸውንም ድንቅ ነገር ሁሉ እናገራለሁ! በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ለስምህ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ። አንተ በምትገለጥበት ጊዜ ጠላቶቼ ወደ ኋላ ይመለሳሉ፤ ተሰናክለውም ከፊትህ ይጠፋሉ። በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ ትክክለኛ ፍርድን ፈራጅ ነህ። የእኔንም ጉዳይ በማየት መብቴን ጠብቀህ በቅን ትፈርድልኛለህ። አሕዛብን ገሠጽክ፤ ክፉዎችንም አጠፋህ፤ ስማቸውንም ለዘለዓለም ደመሰስህ። ጠላቶቻችን ለዘለዓለም ጠፍተዋል፤ ከተሞቻቸውንም ደምስሰሃል፤ መታሰቢያቸውም ጠፍቶአል።