አሁን ግን በመረጥከው ንጉሥ ላይ ተቈጥተሃል፤ ተለይተኸዋል፤ ጥለኸዋልም። ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አፍርሰሃል፤ ዘውዱንም በዐፈር ላይ ጥለኸዋል። ቅጽሮቹን አፈራርሰሃል፤ ምሽጎቹንም ደምስሰሃል። የመንገድ ተላላፊዎች ሁሉ ንብረቱን ይዘርፋሉ፤ የጐረቤቶቹ መሳለቂያ ሆኖአል። ድልን ለጠላቶቹ ሰጥተህ፥ እንዲደሰቱ አደረግኻቸው። የመዘዘውን ሰይፍ እንዲመልስ አድርገኸዋል፤ በጦርነትም አልረዳኸውም። በትረ መንግሥቱን ነጠቅኸው፤ ዙፋኑንም በመሬት ላይ ጣልክበት። ያለ ዕድሜው አስረጀኸው፤ በኀፍረትም ሸፈንከው። እግዚአብሔር ሆይ! የምትሰወረው ለዘለዓለም ነውን? ቊጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው? ዕድሜዬ ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ አስብ፤ ሰውን ሁሉ የፈጠርከው ለከንቱ ነውን? ሰው ሞት ሳይደርስበት እንዲሁ ለመኖር እንዴት ይችላል? ወደ መቃብር ሳይወርድ ሊቀርስ እንዴት ይችላል? ጌታ ሆይ! የቀድሞዎቹ የፍቅርህ ማረጋገጫዎች የት አሉ? ለዳዊት የሰጠኸውስ የተስፋ ቃል የት ነው? እኔ አገልጋይህ የቱን ያኽል እንደምሰደብ፥ የሕዝቦችን ሁሉ ስድብ ታግሼ እንደምኖር አስብ እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶችህ የመረጥከውን ንጉሥ ይሰድባሉ፤ በሄደበት ሁሉ ያፌዙበታል። እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
መጽሐፈ መዝሙር 89 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 89:38-52
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች