እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ዘወትር እዘምራለሁ፤ እውነተኛነትህንም ለትውልድ ሁሉ እገልጣለሁ። ፍቅርህ ለዘለዓለም እንደሚጸናና ታማኝነትህን እንደ ሰማይ እንደሚመሠረት እናገራለሁ። አንተ አስቀድመህ፦ “ከመረጥኩት ሰው ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፤ ለአገልጋዬ ለዳዊት የተስፋ ቃል ሰጠሁት” ብለህ ነበር፤ የሰጠኸውም የተስፋ ቃል “ዘርህ ለዘለዓለም ይነግሣል፤ ትውልድህንም ለዘለዓለም አጸናዋለሁ” የሚል ነው። እግዚአብሔር ሆይ! ሰማያት ድንቅ ሥራዎችህን ያመስግኑ የሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤም ታማኝነትህን ከፍ ከፍ ያድርጉ። በሰማይ እግዚአብሔርን የሚመስል የለም፤ ከሰማይ መላእክትም መካከል ከእግዚአብሔር ጋር የሚስተካከል የለም። በሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤ መካከል እግዚአብሔር የተፈራ ነው፤ በዙሪያውም ካሉት ሁሉ ታላቅና አስፈሪ ነው። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እንደ አንተ ያለ ኀያል ማነው! አንተ በሁሉ ነገር ታማኝ ነህ። አንተ የባሕሩን መናወጥ በሥልጣንህ ታዛለህ፤ ማዕበሉንም ጸጥ ታደርጋለህ። ረዓብ የተባለውን አውሬ ቀጥቅጠህ ገደልከው፤ በታላቁ ኀይልህ ጠላቶችህን በታተንካቸው። ሰማይና ምድር የአንተ ናቸው፤ ዓለምንና በውስጡ ያሉትን ሁሉ የፈጠርክ አንተ ነህ። አንተ ሰሜንና ደቡብን ፈጠርክ፤ የታቦርና የሔርሞን ተራራዎች ለአንተ በደስታ ይዘምራሉ። ሥልጣንህ እጅግ የበረታ ነው፤ ኀይልህም እጅግ ታላቅ ነው። ጽድቅና ትክክለኛ ፍርድ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤ ፍቅርና ታማኝነት ከአንተ ጋር ናቸው። ጌታ ሆይ! የምስጋና መዝሙር የሚያቀርቡልህና በቸርነትህ ብርሃን የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው። በስምህ ቀኑን ሙሉ ይደሰታሉ፤ የማዳን ኀይልህም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል። ገናናው ኀይልህ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ በቸርነትህም ብርታታቸው እያደገ ይሄዳል። አምላካችንና ንጉሣችን የእስራኤል ቅዱስ ሆይ! አንተ በእውነት ጋሻችን ነህ።
መጽሐፈ መዝሙር 89 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 89:1-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
YouVersion የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን ይጠቀማል። የእኛን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በግለሰብነት መመሪያችን ላይ እንደተገለጸው የእኛን የኩኪዎች አጠቃቀም ተቀብለዋል
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች