የእርሱ ሕዝቦች ግን በልዑል እግዚአብሔር ላይ ዐመፁ፤ ተፈታተኑትም፤ ትእዛዞቹንም አልፈጸሙም። ይልቁንም እንደ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና ከዳተኞች ሆኑ፤ እንደ ተጣመመ ፍላጻ የማያስተማምኑ ሆኑ። የአሕዛብ አምልኮ በሚፈጽሙባቸው ስፍራዎቻቸው እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ በጣዖቶቻቸውም አስቀኑት። እግዚአብሔርም በሰማ ጊዜ ተቈጣ፤ ሕዝቡንም ፈጽሞ ተዋቸው። በሴሎ በሰዎች መካከል ይኖርባት የነበረችውን ድንኳኑን ተዋት። የኀይሉና የክብሩ መታወቂያ ምልክት የነበረችውን የቃል ኪዳን ታቦት፥ ጠላቶች ማርከው እንዲወስዱአት አደረገ። የራሱን ሕዝብ ተቈጣ፤ በሰይፍ እንዲገደሉም አደረገ። ጐልማሶች ሁሉ በእሳት ተቃጥለው ሞቱ፤ ልጃገረዶችም የጋብቻቸውን ደስታ ሳያዩ ተቀጩ። ካህናት ሁሉ በሰይፍ ተገደሉ፤ ሚስቶቻቸውም ሊያለቅሱላቸው አልቻሉም። በመጨረሻም እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው ተነሣ፤ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ድፍረት እንደሚሰማው ጀግና ሆነ። ጠላቶቹ ተሸንፈው ወደ ኋላ እንዲሸሹና ዘለዓለማዊ ኀፍረት እንዲከናነቡ አደረገ። የዮሴፍን ተወላጆች ናቀ፤ የኤፍሬምንም ነገድ አልመረጠም። ነገር ግን የይሁዳን ነገድና በጣም የሚወዳትን የጽዮንን ተራራ መረጠ። በዚያም በሰማይ ያለውን ቤቱን የምትመስለውን መቅደሱን ሠራ፤ ለዘለዓለም የምትኖርና እንደ ምድር የጸናች አደረጋት። ባሪያውን ዳዊትን መረጠ፤ ከበጎች መሰማሪያም ወሰደው፤ ከበጎች እረኝነት አውጥቶም፥ የእስራኤል ንጉሥና የእግዚአብሔር ሕዝብ ጠባቂ አደረገው። ዳዊትም በፍጹም ቅንነት ጠበቃቸው፤ በጥበብም መራቸው።
መጽሐፈ መዝሙር 78 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 78:56-72
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos