እግዚአብሔር ምሕረት ማድረጉን ረስቶአልን? ቊጣውስ ርኅራኄውን ገታውን?” ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እኔን ያስጨነቀኝ በታላቁ ኀይልህ እኛን ከመርዳት ማቆምህ ነው። እግዚአብሔር ሆይ! ያከናወንካቸውን ታላላቅ ሥራዎች አስታውሳለሁ፤ ባለፉት ዘመናት ያደረግኻቸው ተአምራት ትዝ ይሉኛል። ሥራዎችህን በጥሞና አሰላስላለሁ፤ ለድርጊቶችህም ከፍ ያለ ግምት እሰጣለሁ። አምላክ ሆይ፥ አንተ የምታደርገው ሁሉ ቅዱስ ነው፤ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማነው?
መጽሐፈ መዝሙር 77 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 77:9-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos