የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 77:9-13

መጽሐፈ መዝሙር 77:9-13 አማ05

እግዚአብሔር ምሕረት ማድረጉን ረስቶአልን? ቊጣውስ ርኅራኄውን ገታውን?” ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እኔን ያስጨነቀኝ በታላቁ ኀይልህ እኛን ከመርዳት ማቆምህ ነው። እግዚአብሔር ሆይ! ያከናወንካቸውን ታላላቅ ሥራዎች አስታውሳለሁ፤ ባለፉት ዘመናት ያደረግኻቸው ተአምራት ትዝ ይሉኛል። ሥራዎችህን በጥሞና አሰላስላለሁ፤ ለድርጊቶችህም ከፍ ያለ ግምት እሰጣለሁ። አምላክ ሆይ፥ አንተ የምታደርገው ሁሉ ቅዱስ ነው፤ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማነው?