የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 73:25-28

መጽሐፈ መዝሙር 73:25-28 አማ05

በሰማይ ከአንተ ሌላ ማን አለኝ? በምድርስ አንተን ካገኘሁ ሌላ ምን እሻለሁ? አእምሮዬና ጒልበቴ ሊደክሙ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን እስከ ዘለዓለም ብርታቴና አለኝታዬ ነው። እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉ፤ አንተን የሚክዱህን ሁሉ ትደመስሳቸዋለህ። ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረቤ መልካም ነው፤ የአንተን ሥራ ሁሉ ለማብሠር እንድችል አንተን ጌታ አምላኬን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ።