የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 73:21-26

መጽሐፈ መዝሙር 73:21-26 አማ05

ኅሊናዬን በጣም መረረው፤ ልቤም ተሰበረ። ጌታ ሆይ! እኔ ለአንተ ከእንስሶች የማልሻል፥ ምንም የማይገባኝ አላዋቂ ነበርኩ። ነገር ግን ዘወትር ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤ አንተም ቀኝ እጄን ትይዛለህ። በምክርህ ትመራኛለህ፤ በመጨረሻም በክብር ትቀበለኛለህ። በሰማይ ከአንተ ሌላ ማን አለኝ? በምድርስ አንተን ካገኘሁ ሌላ ምን እሻለሁ? አእምሮዬና ጒልበቴ ሊደክሙ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን እስከ ዘለዓለም ብርታቴና አለኝታዬ ነው።