የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 71:14-18

መጽሐፈ መዝሙር 71:14-18 አማ05

እኔ ግን ዘወትር አንተን ተስፋ አደርጋለሁ፤ በበለጠም መላልሼ አመሰግንሃለሁ። ምንም እንኳ ማስተዋል ቢያዳግተኝ፥ አንደበቴ ስለ ትክክለኛ ፍርድህና ስለ አዳኝነትህ ቀኑን ሙሉ ይናገራል። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! መጥቼ ኀያል ሥራዎችህን ዐውጃለሁ፤ ትክክለኛ ፍርድ የመስጠት ኀይል የአንተ ብቻ መሆኑን እናገራለሁ፤ አምላክ ሆይ! አንተ ከልጅነቴ ጀምረህ አስተማርከኝ፤ ገና አሁንም ድንቅ ሥራህን እናገራለሁ። አምላክ ሆይ! ሥልጣንህን ለሚመጣው ትውልድ፥ ኀይልህንም ለሚመጡት ሁሉ እስክገልጥና አርጅቼ እስክሸብት ድረስ እንኳ አትተወኝ።