መጽሐፈ መዝሙር 63:6-8

መጽሐፈ መዝሙር 63:6-8 አማ05

በመኝታዬም ሆኜ አስታውስሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ የአንተን ነገር አስባለሁ። አንተ ረዳት ስለ ሆንከኝ በጥበቃህ ሥር ተጠልዬ፥ በደስታ እዘምራለሁ። ወደ አንተ እጠጋለሁ፤ ቀኝ እጅህም ቀና አድርጎ ይደግፈኛል።