የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 63:1-6

መጽሐፈ መዝሙር 63:1-6 አማ05

እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደ ተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች። በመቅደስህ ውስጥ አንተን ተመለከትኩ፤ ኀይልህንና ክብርህንም አየሁ። ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ከሕይወት እንኳ የሚሻል ስለ ሆነ አመሰግንሃለሁ። በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አመሰግንሃለሁ፤ ለጸሎትም እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ። ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር በደስታ እዘምርልሃለሁ። በመኝታዬም ሆኜ አስታውስሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ የአንተን ነገር አስባለሁ።

Free Reading Plans and Devotionals related to መጽሐፈ መዝሙር 63:1-6