መጽሐፈ መዝሙር 31:1-4

መጽሐፈ መዝሙር 31:1-4 አማ05

እግዚአብሔር ሆይ! መጠጊያ እንድትሆነኝ ወደ አንተ መጥቻለሁ፤ ስለዚህ እንዳፍር አታድርገኝ፤ በጽድቅህም አድነኝ። ጌታ ሆይ! አድምጠኝ፤ ፈጥነህም በመምጣት አድነኝ፤ መጠጊያ አለትና ጠንካራ ምሽግ ሆነህ አድነኝ። አንተ መጠጊያ ምሽጌ ነህ፤ ስለ ስምህ ስትል ምራኝ፤ የምሄድበትንም መንገድ አሳየኝ። አንተ መጠጊያዬ ስለ ሆንክ ጠላቶቼ ከዘረጉብኝ ወጥመድ አውጣኝ።