የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 25:16-22

መጽሐፈ መዝሙር 25:16-22 አማ05

እኔ ብቸኛና ችግረኛ ስለ ሆንኩ አምላክ ሆይ! ወደ እኔ ተመለስ፤ በጎነትንም አድርግልኝ። ከደረሰብኝ ችግር ሁሉ እንድላቀቅ አድርገኝ፤ ከጭንቀቴም ሁሉ አድነኝ። ችግሬንና ሥቃዬን ተመልከት፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በልልኝ። ጠላቶቼ ምን ያኽል እንደ በዙ እይ፤ ምን ያኽል እንደ ጠሉኝም ተመልከት። ጠብቀኝ፤ አድነኝም፤ አንተን መጠጊያ ስላደረግሁ ኀፍረት እንዲደርስብኝ አታድርግ። አምላክ ሆይ! አንተን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ቅንነትና ቀጥተኛነት እንዲጠብቁኝ አድርግ። አምላክ ሆይ! እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድን!