መጽሐፈ መዝሙር 25:1-5

መጽሐፈ መዝሙር 25:1-5 አማ05

እግዚአብሔር ሆይ! የልቤን ሐሳብ ወደ አንተ አቀርባለሁ። አምላኬ ሆይ! በአንተ እታመናለሁ፤ ጠላቶቼ ድል እንዲቀዳጁ አድርገህ አታሳፍረኝ። በአንተ የሚታመኑት ኀፍረት አይደርስባቸውም፤ ኀፍረት የሚደርስባቸው፥ በአንተ ላይ ለማመፅ የሚጣደፉት ናቸው። አምላክ ሆይ! ዱካህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ። አንተ የምታድነኝ አምላኬ ነህና እውነትህን ተከትዬ እንድኖር አስተምረኝ፤ እኔ ዘወትር የምታመነው በአንተ ነው።