የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 22:1-5

መጽሐፈ መዝሙር 22:1-5 አማ05

አምላኬ! አምላኬ! ለምን ተውከኝ? እኔን ከማዳን የራቅኸው ለምንድን ነው? ከመቃተት ድምፄስ የራቅኸው ለምንድን ነው? አምላኬ ሆይ! በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትሰማኝም፤ በሌሊት እጣራለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም። ሆኖም አንተ በእስራኤል የተመሰገንክ፥ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ የምትገዛ ቅዱስ አምላክ ነህ። የቀድሞ አባቶቻችን በአንተ ተማመኑ፤ በአንተም ስለ ተማመኑ አዳንካቸው። ለእርዳታ ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ አዳንካቸው፤ አንተን በተማመኑ ጊዜ አላሳፈርካቸውም።