የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 18:37-50

መጽሐፈ መዝሙር 18:37-50 አማ05

ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤ ሳላጠፋቸውም ወደ ኋላ አልመለስም። ዳግመኛ እንዳይነሡ አድርጌ እመታቸዋለሁ፤ በእግሬም ሥር ይወድቃሉ። ለጦርነት ኀይልን ትሰጠኛለህ፤ በጠላቶቼም ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህ። ጠላቶቼ ከፊቴ ወደ ኋላ እንዲሸሹ አደረግህ የሚጠሉኝንም ሁሉ አጠፋቸዋለሁ። የሚረዳቸውን በመፈለግ ይጮኻሉ፤ ነገር ግን ማንም አያድናቸውም፤ እግዚአብሔርንም ይጠሩታል፤ እርሱ ግን አይመልስላቸውም። ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ እስኪሆኑ ድረስ አደቃቸዋለሁ፤ በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃም እረግጣቸዋለሁ። ከዐመፀኛ ሕዝብ አዳንከኝ፤ በአሕዛብም ላይ ሾምከኝ፤ የማላውቀውም ሕዝብ ይገዛልኛል። ባዕዳን ያጐነብሱልኛል፤ ዝናዬን እንደ ሰሙም ይገዙልኛል። በፍርሃት ይጨነቃሉ፤ በመንቀጥቀጥም ከምሽጋቸው ወጥተው ወደ እኔ ይመጣሉ። እግዚአብሔር ሕያው ነው! አምላኬ መጠጊያዬ ይመስገን! ያዳነኝም ኀያል አምላክ ከፍ ከፍ ይበል። እርሱ ጠላቶቼን ይበቀልልኛል፤ ሕዝቦችንም ከበታቼ አድርጎ ያስገዛልኛል። ከጠላቶቼም ታድነኛለህ። ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኞችም ታድነኛለህ። እግዚአብሔር ሆይ! ስለዚህ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ። እርሱ ላነገሠው ንጉሥ ታላቅ ድልን ያጐናጽፈዋል፤ ራሱ ለቀባው ዘለዓለማዊ ፍቅሩን ያሳየዋል፤ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘለዓለም ይህን ያደርጋል።