ጠላቶቼን አሳድጄ ያዝኋቸው፤ እስኪጠፉም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም። እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቀቅኋቸው፤ ከእግሬም ሥር ወደቁ። አንተ ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፤ ባላንጦቼ እግሬ ላይ እንዲደፉ አደረግህ። ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው እንዲሸሹ አደረግህ፤ እኔም የሚጠሉኝን አጠፋኋቸው። ለርዳታ ጮኹ፤ የሚያስጥላቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም። ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ አደቀቅኋቸው፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም ረገጥኋቸው። በሕዝብ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤ የሕዝቦች መሪ አድርገህ አስቀመጥኸኝ፤ የማላውቀውም ሕዝብ ተገዛልኝ። የባዕድ አገር ሰዎች ይፈሩኛል፤ እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል። ባዕዳን ፈሩ፤ ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ። እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን! የድነቴ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል። እርሱ በቀሌን የሚመልስልኝ፣ አሕዛብንም የሚያስገዛልኝ አምላክ ነው፤ ከጠላቶቼም የሚታደገኝ እርሱ ነው። አንተ ከባላንጦቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኞች አዳንኸኝ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፤ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም በመዝሙር እወድሳለሁ። እርሱ ላነገሠው ታላላቅ ድሎችን ይሰጣል፤ ጽኑ ፍቅሩንም ለቀባው፣ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይገልጣል።
መዝሙር 18 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 18
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 18:37-50
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos