የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 18:20-27

መጽሐፈ መዝሙር 18:20-27 አማ05

እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄም ንጽሕና ይመልስልኛል። እኔ የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትዬአለሁ፤ ፊቴን ከአምላኬ በመመለስ ክፉ ነገር አላደረግሁም። የእግዚአብሔርን ሕጎች ሁሉ እፈጽማለሁ ሥርዓቱንም ከማክበር ወደ ኋላ አላልኩም። በእርሱ ዘንድ ንጹሕ ነበርኩ፤ ከኃጢአትም ራሴን ጠብቄአለሁ። እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና፥ ዋጋዬን ከፈለኝ። አምላክ ሆይ! ለአንተ ታማኞች ለሆኑት ታማኝ ነህ፤ እውነተኞች ለሆኑትም እውነተኛ ነህ። ለንጹሖች ንጹሕ ነህ፤ ለጠማሞች ግን ተገቢ ዋጋቸውን ትሰጣለህ። ትሑቶችን ታድናለህ፤ ትዕቢተኞችን ግን ታዋርዳለህ።