መጽሐፈ መዝሙር 147:12-14

መጽሐፈ መዝሙር 147:12-14 አማ05

ኢየሩሳሌም ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! ጽዮን ሆይ! አምላክሽን አመስግኚ! እርሱ የበሮችሽን መወርወሪያ አጠንክሮ ይጠብቃል፤ በውስጥሽ ያሉትንም ሕዝቦችሽን ይባርካል። እርሱ ወሰንሽን በሰላም ይጠብቃል፤ በመልካም ስንዴም ያጠግብሻል።