መጽሐፈ መዝሙር 145:14-21

መጽሐፈ መዝሙር 145:14-21 አማ05

የሚንገዳገዱትን ይደግፋል፤ የወደቁትንም ያነሣቸዋል። ሁሉም በተስፋ ወደ አንተ ይመለከታሉ፤ አንተም በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ምግባቸውን ትሰጣቸዋለህ። እጅህን ከፍተህ የእያንዳንዱን ሕያው ፍጥረት ፍላጎት ታረካለህ። እግዚአብሔር በሚያደርገው ሁሉ እውነተኛ ነው፤ በሥራውም ሁሉ ታማኝ ነው። እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥ ማለትም በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። በአክብሮት ለሚፈሩት የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ይሰጣቸዋል፤ ጩኸታቸውንም ሰምቶ ያድናቸዋል። እርሱን የሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤ ክፉዎችን ግን ይደመስሳል። እኔ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ እርሱ የፈጠራቸው ሁሉ ቅዱስ ስሙን ለዘለዓለም ያወድሱ።