መጽሐፈ መዝሙር 143:8-10

መጽሐፈ መዝሙር 143:8-10 አማ05

የምተማመነው በአንተ ስለ ሆነ በየጠዋቱ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ ሕይወቴን በዐደራ ለአንተ ስለ ሰጠሁ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ። እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ስለ ተማጠንኩ ከጠላቶቼ አድነኝ። አንተ አምላኬ ነህ፤ ፈቃድህን እንዳደርግ አስተምረኝ፤ በመልካም ቸርነትህ በደኅና መንገድ ምራኝ።