የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 133:1-3

መጽሐፈ መዝሙር 133:1-3 አማ05

ወንድማማች አብረው ይኖሩ ዘንድ ምንኛ መልካምና ደስ የሚያሰኝ ነው! በአሮን ራስና ጢም ላይ እንደሚፈስስ፥ እስከ ልብሱም ዘርፍ ድረስ እንደሚዘልቅ፥ መልካም መዓዛ እንዳለው የወይራ ዘይት ነው። ከሔርሞን ተራራ ወደ ጽዮን ኰረብቶች እንደሚንጠባጠብ ጤዛ ነው፤ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ የሆነውን ሕይወትና በረከት የሚሰጠው በዚያ ነው።