እግዚአብሔርን የሚፈሩና ትእዛዞቹን በመጠበቅ የሚኖሩ ደስ ይበላቸው። ሠርተህ የምታፈራውን ትመገባለህ፤ ደስታና ሀብትም ታገኛለህ። ሚስትህ በቤትህ እንደ ፍሬያማ የወይን ተክል ትሆናለች፤ ልጆችህም በማእድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ለምለም ቅርንጫፎች ይሆናሉ። እግዚአብሔርን የሚፈራ እንደዚህ የተባረከ ይሆናል። እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ! የኢየሩሳሌምን ብልጽግና በሕይወትህ ዘመን ሁሉ እንድታይ ያድርግህ! የልጆችህን ልጆች ለማየት እንድትበቃ ያድርግህ!
መጽሐፈ መዝሙር 128 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 128:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች