እግዚአብሔር ሆይ! አንድም ታማኝ ሰው ስላልቀረ እባክህ እርዳን፤ ታማኞች ሰዎች በሰው ዘር መካከል ጠፍተዋል። አንዱ ለአንዱ ውሸትን ይናገራል፤ በሚያቈላምጥ አንደበት የሚናገሩትም በሁለት ልብ ነው። እግዚአብሔር ሆይ! የሚያቈላምጡ ከንፈሮችንና የሚመኩ አንደበቶችን ዝጋ። እነርሱ፦ “በመናገራችን የፈለግነውን እናገኛለን፤ እንደ ፈቀድን እንናገራለን፤ ሊከለክለን የሚችል ማን ነው?” ይላሉ። እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል። የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የታመኑ ናቸው፤ በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው። እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ሁልጊዜ ጠብቀን፤ ክፉ ከሆኑት ከዚህ ዘመን ሰዎች አድነን። ክፉ ነገር በሰዎች ዘንድ በሚመሰገንበት ጊዜ ክፉ ሰዎች በኩራት ይመላለሱበታል።
መጽሐፈ መዝሙር 12 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 12:1-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos