የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 116

116
ከሞት የዳነ ሰው ለእግዚአብሔር ያቀረበው ምስጋና
1ጩኸቴንና ልመናዬን ስለ ሰማ
እግዚአብሔርን እወደዋለሁ።
2እርሱን በምጠራው ጊዜ ሁሉ ስለሚሰማኝ፥
በዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጮኻለሁ።
3የሞት አደጋ ዙሪያዬን ከበበኝ፤
የመቃብር አስፈሪ ሁኔታ አሠቀቀኝ፤
በችግርና በሐዘን ተሸነፍኩ።
4በዚያን ጊዜ “አምላክ ሆይ! እባክህ አድነኝ!”
ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽኩ።
5እግዚአብሔር ቸርና እውነተኛ ነው፤
አምላካችን መሐሪ ነው።
6እግዚአብሔር የዋሆች የሆኑትን ይጠብቃል፤
እኔ በተቸገርኩ ጊዜ አድኖኛል።
7እግዚአብሔር መልካም ነገር ስላደረገልኝ፥
ከእንግዲህ ወዲያ አልጨነቅም።
8እግዚአብሔር ከሞት አዳነኝ፤
እንባዬ እንዲቆም አደረገ፤
እግሮቼንም ከመደናቀፍ ጠበቃቸው።
9ስለዚህ ሕያዋን በሚገኙበት
በእግዚአብሔር ፊት እኖራለሁ።
10“እጅግ ተሠቃየሁ” ባልኩበት ጊዜ እንኳ
አንተን ማመኔን አልተውኩም። #2ቆሮ. 4፥13።
11በፍርሃቴ ጊዜ እንኳ
“ማንም የሚታመን የለም” አልኩ።
12ስላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ
ለእግዚአብሔር ምን ውለታ ልመልስ እችላለሁ?
13እግዚአብሔር ስላዳነኝ አመሰግነዋለሁ፤
የወይን ጠጅ መባም አቀርብለታለሁ።
14በሕዝብ ጉባኤ ፊት ተገኝቼ
ለእግዚአብሔር የተሳልኩትን አቀርባለሁ።
15የቅዱሳን ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ
የከበረ ነው።
16እግዚአብሔር ሆይ! እኔ የአንተ ነኝ፤
የብላቴናይቱ አገልጋይህ ልጅ ነኝ፤
እስራቴን ፈተህልኛል።
ከሞት ያዳንከኝ አንተ ነህ።
17የምስጋና መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፤
ወደ አንተም እጸልያለሁ።
18በእርሱ ሕዝብ ጉባኤ ፊት ተገኝቼ
ለእግዚአብሔር የተሳልኩትን አቀርባለሁ፤
19የማቀርበውም በኢየሩሳሌም መካከል
በሚገኘው በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ነው።
እግዚአብሔር ይመስገን!

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ