መጽሐፈ መዝሙር 111
111
ለእግዚአብሔር የቀረበ ምስጋና
1እግዚአብሔር ይመስገን!
በቅኖች ሸንጎና በጉባኤም መካከል
እግዚአብሔርን በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።
2እግዚአብሔር ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርጎአል፤
በእርሱ አስደናቂ ሥራዎች የሚደሰት ሁሉ ያስባቸዋል።
3የእግዚአብሔር ሥራ በክብርና በግርማ የተሞላ ነው፤
ጽድቁም ዘለዓለማዊ ነው።
4እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ነው፤
በአስደናቂ ሥራውም የገነነ ነው።
5ለሚፈሩት ሁሉ ምግባቸውን ያዘጋጅላቸዋል፤
ቃል ኪዳኑንም ከቶ አይረሳም።
6የሕዝቦችን ርስት በመስጠት
ታላቅ ኀይሉን ለወገኖቹ አሳይቶአል።
7የሚያደርገው ሁሉ እውነትና ትክክል ነው፤
ትእዛዞቹም የታመኑ ናቸው።
8እነርሱም ለዘለዓለም የጸኑ ናቸው፤
የተሰጡትም በእውነትና በታማኝነት ነው።
9ለድኾች በልግሥና ይሰጣል፤
ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳኑንም ሰጠ፤
ስሙም ቅዱስና አስፈሪ ነው።
10እግዚአብሔርን መፍራት
የጥበብ መጀመሪያ ነው፤
ትእዛዙን የሚፈጽሙትን ሁሉ
አስተዋዮች ያደርጋቸዋል፤
እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! #ኢዮብ 28፥28፤ ምሳ. 1፥7፤ 9፥10።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 111: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997