የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 110:1-7

መጽሐፈ መዝሙር 110:1-7 አማ05

እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ) “ጠላቶችህን በእግርህ ማረፊያ ሥር እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው። እግዚአብሔር ኀያል ገዢነትህን ከጽዮን አንሥቶ ያሰፋዋል፤ እንዲህም ይልሃል፦ “በጠላቶችህ ላይ ንገሥ።” መግዛት በምትጀምርበት ቀን ሕዝብህ ይገዙልሃል፤ የተቀደሰውን መጐናጸፊያ ደርበህ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት እንደ ጠል ወለድኩህ። እግዚአብሔር “በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም ካህን ትሆናለህ” ብሎ ማለ፤ መሐላውም የማይሻር ነው። እግዚአብሔር በቀኝህ ነው፤ በሚቈጣበት ጊዜ ነገሥታትን ድል ነሥቶ ይሰባብራቸዋል። በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ የጦር ሜዳዎችንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል፤ በምድር ላይ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ይደመስሳል። ንጉሡ ከመንገድ ዳር ካለው ምንጭ ከጠጣ በኋላ፥ ኀይሉን በማደስ በድል አድራጊነት ጸንቶ ይቆማል።