መጽሐፈ ምሳሌ መግቢያ
መግቢያ
መጽሐፈ ምሳሌ፥ በፈሊጣዊና በምሳሌያዊ አነጋገር የተዘጋጀ የሥነ ምግባርና የሃይማኖት ትምህርት ነው። አብዛኛው የሚያወሳው በዕለት ኑሮ ስለሚያጋጥሙ ነገሮች ነው፤ “እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው” የሚለውን መመሪያ በማስገንዘብ ይጀምራል፤ የሚያስተምረውም ሃይማኖታዊ ሥነ ምግባርን ብቻ ሳይሆን፥ ሰው በዕለት ኑሮው ሊፈጽማቸው የሚገባውን መልካም ጠባይና በጎ ሥራ ጭምር ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ትሕትና፥ ስለ ትዕግሥት፥ ስለ ሰብአዊ ርኅራኄና ስለ ታማኝነት ብዙ ትምህርት በምሳሌ ተሰጥቷል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ምሳሌዎችን በምን ዐይነት እንደምንጠቀምባቸው (1፥1-7)
ጥበብን ለመሻት የተሰጠ ምክር (1፥8—7፥27)
ጥበብን በማሞገስ የተነገረ መዝሙር (8፥1—9፥1-18)
የሰሎሞን ምሳሌዎች (10፥1—29፥27)
አጉር የተናገራቸው ንግግሮች (30፥1-33)
የልሙኤል እናት ለልጅዋ ያስተማረችው ትምህርት (31፥1-31)
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997