የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 5:1-5

መጽሐፈ ምሳሌ 5:1-5 አማ05

ልጄ ሆይ! እኔ ወደምነግርህ ጥበብና ማስተዋል አተኲረህ አድምጥ። ይህን ብታደርግ አስተዋይነት ይኖርሃል፤ ንግግርህም ዕውቀት እንዳለህ ይገልጣል፤ የአመንዝራ ሴት ከንፈር የማር ወለላ የሚያንጠባጥብ ይመስላል፤ ንግግርዋም ከዘይት ይልቅ የለዘበ ነው። በመጨረሻ ግን እርስዋ እንደ እሬት የመረረችና ሁለት አፍ እንዳለው ስለታም ሰይፍ የምትቈርጥ ነች። መንገዶችዋ ወደ ሞት የሚያደርሱ ናቸው፤ እርምጃዎችዋም ወደ ሲኦል ይመራሉ።