የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 25:18-22

መጽሐፈ ምሳሌ 25:18-22 አማ05

በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር ሰው የሰይፍ፥ የዱላና የተሳለ ፍላጻ ያኽል ሊጐዳው ይችላል። በመከራ ጊዜ በማይታመን ሰው ላይ መደገፍ በተነቃነቀ ጥርስ እንደማኘክና በተሰበረ እግር እንደ መራመድ ያኽል ነው። ላዘነ ሰው መዝፈን፥ በብርድ ቀን ልብስ የማውለቅና በቊስል ላይ ሆምጣጤ የመጨመር ያኽል የከፋ ነው። ጠላትህ ቢርበው አብላው፤ ቢጠማውም አጠጣው፤ ይህን ብትፈጽም በኀፍረት እሳት እንዲቃጠል ታደርገዋለህ፤ ለአንተ ግን እግዚአብሔር የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።