በጥበብ ቤት ይሠራል፤ በማስተዋልም ጸንቶ እንዲኖር ይደረጋል። ዕውቀት ሲኖር ቤት በከበሩና በሚያምሩ ዕቃዎች ይሞላል። ብርቱ ከመሆን ይልቅ ብልኅ መሆን ይሻላል፤ በእርግጥም ዕውቀት ከኀይል ይበልጣል፤ ለጦርነት ከመሰለፍህ በፊት በጥንቃቄ ዕቅድ ማውጣት ይኖርብሃል፤ ብዙ አማካሪዎች የምታገኝ ከሆነም ማሸነፍህ አይቀርም። ማስተዋል የጐደለው ሰው ጥበብን መገንዘብ አይችልም፤ ሰዎች ቁም ነገር ባለው ጉዳይ ላይ ሲወያዩ እርሱ የሚያቀርበው አስተያየት የለም።
መጽሐፈ ምሳሌ 24 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ምሳሌ 24:3-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos