የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 2:1-5

መጽሐፈ ምሳሌ 2:1-5 አማ05

ልጄ ሆይ! የማስተምርህን ተቀበል፤ ትእዛዞቼንም በልብህ አኑር። የጥበብን ቃል አድምጥ፤ በጥንቃቄም አስተውለው። ማስተዋልን ጥራ፤ ለዕውቀትም ድምፅህን ከፍ አድርግ። ብር ወይም የተሰወረ ሀብት ለማግኘት ጥረት የምታደርገውን ያኽል ተግተህ ጥበብን ፈልጋት። ይህን ሁሉ ብታደርግ እግዚአብሔርን መፍራት ምን እንደ ሆነ ታውቃለህ፤ የአምላክንም ዕውቀት ታገኛለህ።