የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 19:8-23

መጽሐፈ ምሳሌ 19:8-23 አማ05

ጥበብን የሚገበይ ሰው ራሱን ይወዳል፤ ዕውቀትን አጥብቆ የሚይዝ ይበለጽጋል። በሐሰት የሚመሰክር ሰው ሳይቀጣ አይቀርም፤ ሐሰትንም የሚናገር ጥፋት ያገኘዋል። ሞኞች በድሎት መኖር አይችሉም፤ የባሪያ በመኳንንት ላይ ገዢ መሆንማ ምንኛ የከፋ ነው? የቊጣን ስሜት መቈጣጠር አስተዋይነት ነው፤ ለበደለም ይቅርታ ማድረግ ጨዋነት ነው። የንጉሥ ቊጣ እንደ አንበሳ ጩኸት አስፈሪ ነው፤ ከንጉሥ ዘንድ የሚገኝ ሞገስ ግን ሣርን እንደሚያለመልም ጠል ነው። ሞኝ ልጅ አባቱን ወደ ጥፋት ያደርሳል፤ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ ዝናብ አሰልቺ ናት። አንድ ሰው ቤትና ሀብት ከወላጆቹ ሊወርስ ይችላል፤ አስተዋይ ሚስትን የሚሰጥ ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስንፍና እንቅልፍን ያስከትላል፤ ስለዚህም ሰነፍ ሰው ይራባል። ትእዛዝን የሚጠብቅ በሕይወት ይኖራል፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሚንቅ ግን ይጠፋል። ለድኾች የሚሰጥ ለእግዚአብሔር እንዳበደረ ይቈጠራል፤ እግዚአብሔርም የመልካም ሥራውን ዋጋ ይከፍለዋል። የመመለስ ተስፋ ሳላቸው ልጆችህን በልጅነታቸው ቅጣቸው፤ ባትቀጣቸው ግን ለጥፋት አሳልፈህ እንደ ሰጠሃቸው ይቈጠራል። ግልፍተኛ ሰው ቢኖር የግልፍተኛነቱን ዋጋ እንዲያገኝ ተወው፤ አንድ ጊዜ ከችግሩ ልታወጣው ብትሞክር ሌላ ጊዜም እንዲሁ ማድረግህ አይቀርም። ምክርን ብትሰማና ለመማርም ፈቃደኛ ብትሆን የኋላ ኋላ ጥበብ መገብየትህ አይቀርም። ሰዎች ብዙ ነገር ያቅዳሉ፤ ተፈጻሚነትን የሚያገኘው ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ከሰው የሚፈለገው ታማኝነት ነው፤ ሐሰተኛ ከመሆን ይልቅ ድኻ መሆን ይሻላል። እግዚአብሔርን ብትፈራ ረጅም ዕድሜ ይኖርሃል፤ ጒዳት ሳይደርስብህ በደስታና በሰላም ትኖራለህ።