የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:1-9

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:1-9 አማ05

የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ፥ የደስታዬና የሥራዬ አክሊል የሆናችሁ ወንድሞቼ ሆይ! በጌታ ጸንታችሁ ኑሩ። ኤዎድያና ሲንጢኪ እርስ በርሳቸው በጌታ ተስማምተው እንዲኖሩ እለምናቸዋለሁ። አንተም እዚያ ያለኸው ታማኝ የሥራ ጓደኛዬ እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ፤ እነዚህ ሴቶች ከእኔ ጋር ከቀሌምንጦስና ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎችም የሥራ ጓደኞቼ ጋር በመሆን ወንጌልን በማዳረስ ረገድ ተጋድለዋል። ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜም “ደስ ይበላችሁ!” እላለሁ። ደግነታችሁ በሰው ሁሉ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ ጌታ ተመልሶ ሊመጣ ቀርቦአል፤ ስለዚህ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፥ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ። ከሰው ማስተዋል ሁሉ በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አእምሮአችሁን በኢየሱስ ክርስቶስ ይጠብቃል። አእምሮአችሁ በእነዚህ ከሁሉ በሚበልጡና በሚያስመሰግኑ መልካም ነገሮች የተመላ ይሁን፤ በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ፥ ክቡር፥ ትክክለኛ፥ ንጹሕ፥ አስደሳችና ምስጉን የሆኑ ነገሮችን ሁሉ አስቡ። ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን፥ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ሁሉ አድርጉ፤ የሰላም አምላክም ከእናንተ ጋር ይሆናል።