ኦሪት ዘኊልቊ መግቢያ
መግቢያ
ኦሪት ዘኍልቊ እስራኤላውያን የሲናን ተራራ ከለቀቁበት ጊዜ አንሥቶ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ቃል ወደገባላቸው የተስፋይቱ ምድር ምሥራቃዊ ወሰን እስከ ተቃረቡ ድረስ ያለውን አርባ ዓመት ታሪክ ያወሳል። የመጽሐፉ ስም ከታሪኩ ጐላ ብሎ የሚታየውን ክፍል ያመለክታል፤ ይኸውም እስራኤላውያን የሲናን ተራራ ለቀው ከመሄዳቸው በፊት፥ እንዲሁም ከአንድ ትውልድ በኋላ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ በሞአብ ሙሴ ያደረገውን የሕዝብ ቈጠራ ያመለክታል። በሁለቱ የሕዝብ ቈጠራ መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ እስራኤላውያን የከነዓን ደቡባዊ ወሰን ወደ ሆነው ወደ ቃዴስ በርኔ ደርሰው ነበር፤ ይሁን እንጂ በዚያ በኩል ወደ ተስፋይቱ ምድር መግባት አልቻሉም፤ ስለ ሆነም በዚያ አካባቢ ብዙ ዓመቶች ካሳለፉ በኋላ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ወደሚገኘው አገር ሄዱ፤ ከፊሉ ሕዝብ እዚያው ለመኖር ሲወስኑ፥ የቀሩት ግን የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ከነዓን ለመሄድ ዝግጅት አደረጉ።
ኦሪት ዘኍልቊ ብዙ ጊዜ ችግር ሲገጥማቸው የሚፈሩና ተስፋ የሚቈርጡ፥ በእግዚአብሔርና መሪያቸው ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር በመረጠላቸው በሙሴ ላይ የሚያምፁ ሕዝብ ታሪክ ነው። ሕዝቡ ደካሞችና እምቢተኞች ቢሆኑም እንኳ እግዚአብሔር ይንከባከባቸው እንደ ነበር በታሪኩ ተገልጦአል፤ እንዲሁም ሙሴ አንዳንድ ጊዜ ትዕግሥት ቢያጣም፥ ጽኑ እምነት እንደ ነበረውና እግዚአብሔርንና ሕዝቡን በታማኝነት እንዳገለገለ ታይቶአል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
እስራኤላውያን ከሲና ተራራ ተነሥተው ለመሄድ መዘጋጀታቸው 1፥1—9፥23
ሀ. የመጀመሪያው የሕዝብ ቈጠራ 1፥1—4፥49
ለ. የተለያዩ ሕጎችና ደንቦች 5፥1—8፥26
ሐ. ሁለተኛው ፋሲካ 9፥1-23
ከሲና ተራራ ወደ ሞአብ 10፥1—21፥35
በሞዓብ የተፈጸሙ ሁኔታዎች 22፥1—32፥42
ከግብጽ እስከ ሞአብ የተደረገው ጒዞ ባጭሩ 33፥1-49
ዮርዳኖስን ከመሻገር በፊት የተሰጡ መመሪያዎች 33፥50—36፥13
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997