ኦሪት ዘኊልቊ 23:19-20

ኦሪት ዘኊልቊ 23:19-20 አማ05

እግዚአብሔር እንደ ሰው አይዋሽም፤ ሐሳቡንም እንደ ሰው አይለውጥም የሰጠውን ተስፋ ሁሉ ይፈጽማል፤ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያደርጋል። እኔ የተነገረኝ እንድመርቅ ነው፤ እግዚአብሔር ሲመርቅ እኔ የእርሱን ቃል መለወጥ አልችልም።