ሌሎቹ ደግሞ “ከደረሰብን ብርቱ ራብ ሕይወታችንን ለማትረፍ የሚያስችል እህል ለማግኘት ስንል እርሻችንን፥ የወይን ተክላችንንና ቤታችንን ሁሉ መያዣ አድርገን እስከ መስጠት ደርሰናል” ይሉ ነበር። ሌሎችም ደግሞ “ስለ እርሻችንና ስለ ወይን ተክላችን መንግሥት የጠየቀንን ግብር ለመክፈል የገንዘብ ብድር ተበድረናል፤ ከአይሁድ ወገኖቻችን ጋር ዘራችን አንድ ነው፤ የእኛ ልጆች ከእነርሱ ልጆች የሚለዩበት ምንም ነገር የለም፤ ይሁን እንጂ የገዛ ልጆቻችንን ለባርነት አሳልፈን ለመስጠት ተገደናል፤ እንዲያውም ከሴቶች ልጆቻችን አንዳንዶቹ ባሪያዎች ሆነዋል፤ ነገር ግን እርሻችንና የወይን ተክል ቦታችን ስለ ተወሰዱ ኀይል የሌለን ሆነናል” በማለት አቤቱታ አሰሙ።
መጽሐፈ ነህምያ 5 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ነህምያ 5:3-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos