የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ነህምያ 12:27-30

መጽሐፈ ነህምያ 12:27-30 አማ05

የኢየሩሳሌም ከተማ ቅጽር የምረቃ በዓል በተከበረበት ዕለት ሌዋውያኑ በጸናጽል፥ በበገናና በመሰንቆ በዓሉን እንዲያከብሩ ከየሚኖሩበት ስፍራ ተፈልገው መጡ። ይህንንም በዓል ለማክበር የሌዋውያኑ ቤተሰቦች መዘምራን ሁሉ ሰፍረው ከነበሩበት ከኢየሩሳሌም አካባቢና በነጦፋ ከሚገኙት ታናናሽ ከተሞች፥ ከቤትጊልጋል፥ ከጌባዕና ከዓዝማዌት ተሰብስበው መጡ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ስለ ሕዝቡ ራሳቸው ስለ ከተማይቱ በሮችና ስለ ቅጽሩ የማንጻትን ሥርየት ፈጸሙ።