መጽሐፈ ነህምያ 11
11
በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሕዝቦች
1መሪዎቹ መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከሌላውም ሕዝብ መካከል ከየዐሥር ቤተሰብ አንዱ እጅ ቅድስት በሆነችው በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲኖር በዕጣ ተመረጠ፤ የቀሩት ሰዎች ግን በሌሎች መንደሮችና ከተሞች ሁሉ ኑሮአቸውን መሠረቱ፤ 2ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ውስጥ ለመኖር የበጎ ፈቃድ ዝንባሌ ያለውን ሰው ሁሉ አመሰገነ። 3በሌሎች መንደሮችና ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤል ልጆች ካህናቱና ሌዋውያኑ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች በየመንደሮቻቸው ባላቸው ይዞታ ኖሩ። #ነህ. 7፥73።
በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የይሁዳ ምድር መሪዎችም ስም ዝርዝር የሚከተለው ነበር፦
4የይሁዳ ነገድ አባላት፦
የዘካርያስ የልጅ ልጅ የሆነው የዑዚያ ልጅ ዐታያ፤ ሌሎች የቀድሞ አያቶቹ የይሁዳ ልጅ የሆነው የፋሬስ ዘሮች የሆኑትን አማርያን፥ ሸፋጥያንና ማሀላልኤልን ይጨምራሉ።
5የኮልሖዜ የልጅ ልጅ የሆነው የባሩክ ልጅ ማዕሤያ ሌሎች የቀድሞ አባቶቹ የይሁዳ ልጅ የነበረው የሼላ ዘሮች የሆኑትን ሐዛያን፥ ዓዳያን፥ የዮያሪብንና ዘካርያስን ይጨምራል።
6ከፋሬስ ዘሮች መካከል በጀግንነታቸው ታዋቂዎች የሆኑ 468 ሰዎች በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆኑ።
7የብንያም ነገድ አባላት፦
ሳሉ፥ የመሹላም ልጅ፥ የዮዔድ ልጅ፥ የፐዳያ ልጅ፥ የቆላያን ልጅ፥
የማዕሤያን ልጅ፥ የኢቲኤልን ልጅ፥ የሻዕያን ልጅ፥
8የሳሉ የቅርብ ዘመዶች የሆኑ፦
ጋባይና ሳላይ፥ በድምሩ 928 ብንያማውያን በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። 9የዚክሪ ልጅ ኢዩኤል መሪያቸው ሲሆን፥ የሀስኑአ ልጅ ይሁዳ በማዕርግ ሁለተኛ የሆነ የከተማይቱ ባለሥልጣን ነበር።
10ካህናት፦
ይዳዕያ የዩያሪብ ልጅ፥ የያኪን ልጁ፥ 11ሠራያ፥ የሒልቅያ ልጅ፥ የመሹላም ልጅ፥ የጻዶቅ ልጅ፥ የመራዮት ልጅ፥ የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የነበረው የአሒጡብ ልጅ፥ 12ከዚህም ጐሣ ውስጥ በአጠቃላይ 822 አባላት በቤተ መቅደስ ውስጥ አገልጋዮች ነበሩ።
ዓደያ የየሮሖም ልጅ፥ የፐላልያ ልጅ፥ የአምጺን ልጅ፥ የዘካርያስ ልጅ፥ የፓሽሑር ልጅ፥ የማልኪያን ልጅ፥ 13ከዚህም ጐሣ ውስጥ ባጠቃላይ 242 የቤተሰብ መሪዎች ነበሩ።
አማሽሳይ የዐዛርኤል ልጅ፥ የአሕዛይ ልጅ፥ የመሺሌሞት ልጅ፥ የኢሜር ልጅ፥ 14የእርሱም ወንድሞች ስመጥር ወታደሮች የሆኑት አባላት ብዛት 128 ነበር፤ መሪያቸውም ዛብድኤል ተብሎ የሚጠራ የሐጌዶሊም ልጅ ነበር።
15ሌዋውያን፦
ሸማዕያ የሐሹብ ልጅ፥ የዓዝሪቃም ልጅ፥ የሐሻብያን ልጅ፥ የቡኒን ልጅ፥
16ሻበታይና ዮዛባድ ተብለው የሚጠሩ የሌዋውያን መሪዎች ከቤተ መቅደስ በስተውጭ ለሚሠራው ነገር ሁሉ ኀላፊዎች ነበሩ።
17ማታንያ የሚካ ልጅ፥ የዘብዲ ልጅ፥ የመዘምራን አለቃ የነበረው የአሳፍ ልጅ፥ የእርሱ ምክትል የነበረው የባቅቡቅያ ልጅና፥ የሻሙዐ ልጅ የነበረው ዐብዳ፥ የጋላል ልጅ፥ የዩዱቱን ልጅ፥
18ከሌዋውያኑም ወገን በአጠቃላይ 284 ሰዎች በቅድስቲቱ በኢየሩሳሌም ከተማ ይኖሩ ነበር።
19የቤተ መቅደስ ዘበኞች፦
ዓቁብ፥ ጣልሞንና ዘመዶቻቸው በአጠቃላይ 172 ነበሩ።
20በተረፈ ሌሎቹ እስራኤላውያን፥ ካህናትና ሌዋውያን በየርስታቸው በሌሎቹ የይሁዳ ከተሞችና መንደሮች ይኖሩ ነበር። 21የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች የኢየሩሳሌም ከተማ አንዱ ክፍል በሆነው ዖፌል ተብሎ በሚጠራው ኮረብታ ላይ ይኖሩ ነበር፤ ጺሐና ጊሽፓ ተብለው የሚጠሩም ሰዎች የእነርሱ አለቆች ነበሩ።
22በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ዑዚ የባሂ ልጅ፥ የሖሻብያ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ነበር። ዑዚ የቤተ መቅደስ መዘምራን ኀላፊ የነበረው የአሳፍ ዘር ነበር። 23በየዕለቱ የሚቀርበውንም መዝሙር ቅደም ተከተል ተራ በማስያዝ ረገድ ከንጉሡ የተሰጠ ትእዛዝ ነበር።
24ከይሁዳ ነገድ የዛራ ጐሣ ተወላጅ የሆነው የመሼዛቤል ልጅ ፐታሕያ የእስራኤልን ሕዝብ በሚመለከት ጉዳይ የፋርስ ንጉሥ እንደ ራሴ ነበር።
በሌሎች መንደሮችና ከተሞች የሚኖር ሕዝብ
25መንደሮቹንና እርሻዎቹን በተመለከተ ከይሁዳ ነገድ መካከል አንዳንዶቹ በቂርያት አርባዕና በመንደሮችዋ፥ በጊቦንና በመንደሮችዋ በይቀብጽኤልና በመንደሮችዋ፥ 26እንዲሁም ኢያሱ፥ ሞላዳ፥ ቤትጳሌጥና፥ 27ሐጻርሹዓል ተብለው በሚጠሩ ከተሞች ይኖሩ ነበር፤ ቤርሳቤህና በዙሪያዋ የሚገኙ መንደሮችም የእነርሱ መኖሪያዎች ነበሩ፤ 28በጺቅላግ ከተማም በተለይ በመኮናና በአካባቢዋ በሚገኙት መንደሮች፥ 29በዔንሪሞን፥ በጸርዓ፥ በያርሙት፥ 30በዛኖሐ፥ በዐዱላምና በእነዚህም ከተሞች አጠገብ በሚገኙት መንደሮች ሁሉ ይኖሩ ነበር፤ ላኪሽና በአቅራቢያዋ የሚገኙ የእርሻ ቦታዎች፥ ዐዜቃና የአካባቢዋ መንደሮች ሁሉ የእነርሱ መኖሪያዎች ነበሩ፤ በዚህ ዐይነት የይሁዳ ሕዝብ መኖሪያ በደቡብ ከቤርሳቤህ፥ በሰሜን ከሂኖም ሸለቆ በመለስ ባለው ክልል ውስጥ ነበር።
31የብንያም ነገድ ተወላጆች መኖሪያዎች ደግሞ በጌባዕ፥ በሚክማስ፥ በዐይ፥ በቤትኤልና በአካባቢዋ በሚገኙ መንደሮች ነበር፤ 32ዐናቶት፥ ኖብ፥ ዓናንያ፥ 33ሐጾር፥ ራማ፥ ጊታይም፥ 34ሐዲድ፥ ጸቦዒም፥ ነባላጥ፥ 35ሎድና፥ ኦኖ፥ እንዲሁም “የእጅ ጥበብ ሠራተኞች ሸለቆ” ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ሁሉ የእነርሱ መኖሪያዎች ነበሩ። 36በይሁዳ ክፍለ ግዛት ከሚኖሩት የሌዋውያን ቡድኖች መካከል አንዳንዶቹ ከብንያም ሕዝብ ጋር እንዲኖሩ ተደረገ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ነህምያ 11: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997